ስለ ማይጨው ክሊኒክ
ዘመናትን የተሻገረ፣ ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት
Our Story
ታሪክን አክብረን፣ በዘመናዊ የሕክምና ጥበብ እናገለግላለን
ማይጨው ክሊኒክ በኢትዮጵያ የሕክምና ታሪክ ውስጥ የራሱ አሻራ ያለው አንጋፋ ተቋም ሲሆን፤ በ1962 ዓ.ም በሦስት ዝነኛ እና በሀገራችን የሕክምና ዘርፍ ግንባር ቀደም በሆኑ ባለሙያዎች ፕሮፌሰር ጀማል አብዱልቃድር፣ ፕሮፌሰር ደምሴ ሃብቴ እና ዶ/ር አዱኛ መኮንን ተመሰረተ።
እነዚህን እንቁ እና የመጀመሪያ ባለሙያዎች ከሚሰሩበት ሆስፒታል ውጪ ሊገኙ የሚችሉት አሁን በተከፈተው የግል ክሊኒክ ወይም በአሁኑ ጊዜ ማይጨው የሚባለው ክሊኒክ ስለነበር የንጉሰ ነገስቱ ልጆች እና የልጅ ልጆች ቀጠሮ አስይዘው በዚሁ ክሊኒክ ይታከሙ ነበር።
ክሊኒኩ በእነዚህ አንጋፋ ባለሙያዎች ተመስርቶ ስራውን ሲጀምር ስሙ የግል ክሊኒክ በሚል መጠሪያ ሲስራ ከቆየ በኋላ ሌላ ክሊኒክ መከፈት ሲጀምር ማይጨው ክሊኒክ የሚል ስያሜ ተሰጠው።
ስያሜ የተሰጠው አሁን መስቀል አደባባይ የሚባለው በፊት ማይጨው አደባባይ ይባል ስለነበር ስያሜውን የወሰደው ከዚሁ ስያሜ ነው።
በአሁኑ ወቅት በ ዶ/ር ግርማ አዳል ባለቤትነት እና ስራ አስኪያጅነት ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት የታወቀበትን ጥራት ያለው ዘመናዊ የወንዶች የግርዛት አገልግሎት ለህጻናት ፣ ለወጣቶች እና አዋቂ ወንዶች በመስጠት በሃገሪቱ ታዋቂነትን አትርፏል።
Our Process
የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት የሚከተሉትን ቅደም ተከተሎች ይከተሉ
1. ቀጠሮ ይያዙ
ለሕክምናዎ ምቹ የሆነ ሰዓት በዌብሳይታችን ፣ በስልክ ወይም በአካል በመምጣት ያስይዙ።
2. ምርመራ ያድርጉ
ምርመራና እና ቀላል ቀዶ ጥገና ያግኙ።
3. ፈውስ ያግኙ
ዘመናትን በተሻገረ ልምድ የተሟላ የሕክምና እርዳታ ያግኙ።
The Goal
የእኛ ተልዕኮ
ለታካሚዎቻችን ጥራት ያለው ህክምና በተመጣጣኝ ክፍያ በዘመናዊ መሳሪያዎች የታገዘ የህክምና አገልግሎት መስጠጥ።
The Outlook
የእኛ ራዕይ
በኢትዮጵያ ቀዳሚ እና ተመራጭ የግል የሕክምና ተቋም በመሆን ጤናማ ማህበረሰብ እንዲገነባ የድርሻችንን መወጣት እና በክልሎችም ማስፋፋት ነው።
Our Specialized Services
ልዩ አገልግሎቶቻችን
በማይጨው ክሊኒክ የጠቅላላ የሕክምና አገልግሎት ከመስጠቱም በላይ በአሁኑጊዜ እጅግ የታወቀበትን የወንዶች የግርዛት አገልግሎት በሃገር ውስጥ ተወዳዳሪ በማይገኝለት ዘመናዊ የቀለበት መሳሪያ አስተማማኝ ንጽህና ያለው የግርዛት አገልግሎት ለህጻናት ፣ ለወጣቶች እና ለአዋቂ ወንዶች ይሰጣል። በተለይ አዋቂ ወንዶችን በሚስጥራዊ ቀጠሮ ስለምናስተናግድ የት ልሂድ ፣ ማንን ላማክር ብሎ መጨነቅ የለብዎትም። በአድራሻችን ወይም በስልካችን ደውለው ቀጠሮ ማስያዝ ብቻ በቂ ነው። ወንድ ልጅዎ የትም ይወለድ የት ለግርዛት ግን ማይጨው ክሊኒክ ያለጥርጥር ተመራጭ ነው። ሌላ ቦታ ተገርዞ የተበላሸ ካለ እኛ ጋር ባአግባቡ ይስተካከላል።
ለተሟላ ጤናዎ እና ለቤተሰብዎ ደህንነት ቀዳሚ ምርጫዎ!
ማይጨው ክሊኒክ ከ1962 ዓ.ም ጀምሮ ጥራት ያለውን የጠቅላላ ሕክምና እና የወንዶች ግርዛት አገልግሎት በጥራት እና በስፋት እየሰጠ ይገኛል። ጤናዎ የእኛ ስኬት ነው!